መዝሙር 31 ስብሐት ለአምላክ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ስብሐት ለአምላክ ስብሐት ለአምላክ
ስብሐት ስብሐት ለአምላክ በአርያም
ስብሐት ስብሐት ስብሐት ለአምላክ
በአርያም በአርያም በአርያም በአርያም።
ሰላም በምድር በምድር ሰላም
ሰላም በምድር ሰላም ሰላም በምድር
ለሰዎችም ያምላክ ሥምረት ይሁን
ለሰዎችም ያምላክ ሥምረት ይሁን
ለሰዎችም ያምላክ ሥምረት ይሁን።
ስብሐት ለአምላክ በአርያም
ሰላምም በምድር ለሰዎችም የአምላክ ሥምረት
፪፡ እነሆ ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን ደስታ
የምሥራች እነግራችሁአለሁ አትፍሩ።
ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም
ክርስቶስ ጌታ የሆነው ተወልዶላችኋል።
ስብሐት ለአምላክ ስብሐት ለአምላክ
ለአምላክ በአርያም
ስብሐት ስብሐት ስብሐት ለአምላክ በአርያም
በአርያም በአርያም አርያም።
ይህም ምልክት ይሆንላችኋል
ሕፃን በጨርቅ ተጠቅልሎ
በጨርቅ ተጠቅልሎ
በግርማ በበረት ላይ ተኝቶ ታገኛላችሁ።
ስብሐት ለአምላክ . . .።