መዝሙር 71 የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ቤዛ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ቤዛ
የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ቤዛ
ወገኖቹን ሁሉ በራሱ ደም ገዛ
ወገኖቹን ሁሉ በራሱ ደም ገዛ።
፪፡ የሐሰት ምስክር አቁመው ከሰሱት
የሐሰት ምስክር አቁመው ከሰሱት
በሞት እንዲቀጣ ሁሉም ፈረዱበት
በሞት እንዲቀጣ ሁሉም ፈረዱበት።
፫፡ ጲላጦስ ገረፈው በሰንሰለት አስሮ
ጲላጦስ ገረፈው በሰንሰለት አስሮ
ከሮማዊ መንግሥት እንዲኖር ተፋቅሮ
ከሮማዊ መንግሥት እንዲኖር ተፋቅሮ።
፬፡ በብርሃን ዙፋን ላይ የቆሙት እግሮቹ
በብርሃን ዙፋን ላይ የቆሙት እግሮቹ
በችንካር ላይ ሆነው ምንም አልሰለቹ
በችንካር ላይ ሆነው ምንም አልሰለቹ።
፭፡ ድንግል አልቻለችም ዕንባዋን ልትገታ
ድንግል አልቻለችም ዕንባዋን ልትገታ
እያየች በመስቀል ልጅዋ ሲንገላታ
እያየች በመስቀል ልጅዋ ሲንገላታ።
፮፡ የብርሃን አክሊልን ለሰማዕት ያደለ
የብርሃን አክሊልን ለስማዕት ያደለ
የሾህ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ
የሾህ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ።