መዝሙር 395 የሱስ እኔን ተቀበለኝ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የሱስ እኔን ተቀበለኝ
ዘወትር ተንከባከበኝ፤
ጉድለት እንኳ ቢኖርብኝ፥
ለዘላለም ያንተ ነኝ።
ሕይወትና ኃይል አጣለሁ፥
እወድቃለሁ ሁሉ ቀን፤
ባንተ ብቻ ተጥያለሁ፥
ከእናቴ ማኅፀን።
፪፡ እኔ አንድ ምስኪን ድሀ ነኝ
አንተ ሀብታም ጌታ ነህ፤
አንተም ከመሞት አዳንኸኝ፥
ቅጣቴን ተቀብለህ።
ኃጢአቴም ቢያሰፈራኝ፥
ዓይኔን ወደ አንተ ሳብ፤
አንተ ከርሱ ልታጠራኝ፥
አፍስሰሃል የደም ላብ።
፫፡ የሱስ ሆይ የፈጸምክልኝ
ለዘላለም በቂ ነው፤
ሕግህም እንዳይፈርድብኝ።
አንተ ራስህ ፈጸምኸው።
አንተ ስትነግረኝም፥
አምኜ ልቀበለው።
ሌላ አያስፈልገኝም፥
ጸጋህን ላመስግነው።