መዝሙር 73 ክርስቶስ የእኛ መመኪያ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ክርስቶስ የእኛ መመኪያ
በመስቀል ተሰቅሎልናል
ነፍሳችንን ለማውጣት ሲል
ወረደልን ወደ ሲኦል።
በታላቅ ግርማ ሲነሣ
ድል የእኛ ሆኖልናል።
፪፡ ምስጋና ይሁነው ለአብ
ስለ ላከልን የሱስን
መድኃኒት እንዲሆንልን
ከሞት ፍርድ እንዲያድነን።
ስለኛ የተሠዋው በግ
በከበረ ደሙ ገዛን።
፫፡ ባንተ መከራና ሥቃይ
ተከፈተ የሰማይ ቤት
እኛም እንናፍቃለን
መጥተን ክብርህን ልናይ።
የመንፈስ ሥቃይ ከሚሆን
ከሥጋ ምኞች ጠብቀን።
፬፡ አማላጅ አለን ከአብ ዘንድ
የሚያስተሰርይ ኃጢአት
እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
የኛ ሊቀ ካህናት።
ወደ ኃያል አምላካችን
በሙሉ እምነት እንቅረብ።
፭፡ ወንጌል የሚለው ጽደቁ ነው
ሳልጠራጠር አምናለሁ
የሱስ የዓለም ቤዛ
ሆኖ መምጣቱን አውቃለሁ።
ቅዱስ ቃሉ መሪ ሁኖኝ
በሰማይ ቤት እገባለሁ።