መዝሙር 562 እንደሚያበራ ጧት ፀሐይ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ እንደሚያበራ ጧት ፀሐይ
ልክ እንደሚያምር ጤዛ
የየሱስ የከበረ ድምፅ
ያጽናናል ይደግፋል።
ድምፁን ጆሮዬ ሲሰማ
ጨለማው ተወገደ
ሰማያዊ ጣፋጭ ዜማ
ደስታና ሐሴት ሰጠኝ።
ብሩህ ተስፋ ላዘኑ ለደከሙ
ና ወደሱ እረፍት ታገኛለህ።
፪፡ የመዳን መዝሙር ሲዘመር
በልቤ ውስጥ ሰማሁኝ
የሱስ ዘላለም ድል ነሥቷል
አስፈሪው ጨለማ።
በለዘብታ ድምፅ ሰማሁት
ችግረኛን ለመርዳት
ክቡር ሕያው መድኅኔ
ከልቤ ላወድስህ።
ብሩህ ተስፋ . . . ።
፫፡ ተስፋው መልህቃችን ነው
በጽናት የሚያቆመን
ተስፋው ንጽሕናን ይሰጣል
በደሙ ያነጻናል።
የመምጣቱ የተስፋ ቃል
ልቤ እንዴት ይናፍቃል
በትዕግሥት ስትጠብቀው
ጌታን ለመገናኘት።
ብሩህ ተስፋ . . . ።