መዝሙር 380 የጸዮን እስረኞችን ሲፈታ ጌታ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የጸዮን እስረኞችን ሲፈታ ጌታ
እንደሚያልሙ ሰዎች ነበርን እኛ።
አፋችን መላ በደስታ በዕልልታ፥
ታላቅ ሥራ ፈጸመልን ጌታ።
ድምፅህን ከፍ አድርግ ዘምር ወደ ላይ
ውዳሴን አቅርብ ለንጉሠ ሰማይ፥
ጌታ የጽዮን እስረኞችን ሲፈታ፥
እንደሚያልሙ ሰዎች ነበርን እኛ።
፪፡ በዚያን ጊዜ እያነቡ የዘሩ
አዝመራቸውን በደስታ አጨዱ።
ነዶአቸውን በሰላም አሰሩ፥
ከሰማይ ንጉሥ ክብርን አገኙ።
ድምፅህን ከፍ . . .።
፫፡ በደስታ መዝሙራቸው አስተጋባ
አምላክ ታላቅ ሥራ ስለ ሠራ፥
ጭንቃቸውን በረድኤቱ ለወጠ።
ለሕዝቡ የሰላም በር ከፈተ።
ድምፅህን ከፍ . . .።