መዝሙር 363 ደካሞች ኑ ሁላችሁ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ደካሞች ኑ ሁላችሁ
ሸክማችሁ የከበደ።
ዕረፍትና ሕይወትም
ባባቴ ቤት አለና።
ታግሦ የኔን ቀንበር
የሚሸከም ሰው ቢኖር።
፪፡ የኔ ቀንበር ልዝብ ነው
ሸክሜም በጣም ቀላል ነው።
ትሑት ሰውም እኔ ነኝ
ልቤም ደግሞ የዋህ ነው።
በእኔ የሚያምን ሰው።
በነፍሱ ዕረፍት አለው።
፫፡ የሕይወት ውኃ ይህ ነው
ከጎኔ የፈለቀው።
የተጠማ ሰው ቢኖር
ይምጣ ከዚያ ይጠጣ።
የተጠማ ሰው ቢኖር
ይምጣ ከዚያ ይጠጣ።