መዝሙር 354 የአምላክ ዕቅፍ ተከፍቶአል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የአምላክ ዕቅፍ ተከፍቶአል
አንተን ሊቀበልህ፤
በስምህም ይጠራሃል
በፍቅሩ ፈለገህ።
እጁንም ዘርግቶልሃል
በታላቅ ምሕረት፤
ለአንተ ተዘጋጅቶአል
ስፍራ በሠርጉ ቤት።
፪፡ በዚህ በዓለም በረሃ
ሰላም አታገኝም፤
ከሕይወት ምንጭ ጥሩ ውኃ
እንዴት አትመኝም፤
በሌላ ምንጭ የልብህ ጥም
ሊረካ አይችልም፤
መድኃኒት ያለ የሱስ ስም
አልተገኘልህም።
፫፡ ርስትህን ሁሉ በትነህ
መሞት ያስፈራሃል፤
በቤቱ ግን ቸር አባትህ
አንተን ይጠብቃል።
የሰርግ ልብስና ቀለበት
በዚያ ይቆይሃል፤
በከንቱ ሁሉን ለመስጠት
አባትህ ወዶአል።
፪፡ የጠፋው ልጅ ወዳባቱ
ቢሄድ በንስሐ፥
በማይመረመር ምሕረቱ
ያወርሰዋል ደስታ።
በቤቱ ሁሉ ግሩም በዓል
ዕልልታ መዝሙርም፥
በዚያ ቀን ይደረጋል
ደስታው አይተረክም።