መዝሙር 342 ያለህን ለጌታ አስረክብ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ያለህን ለጌታ አስረክብ
የወጣት ጉልበትህን፤
ባዲስ ሕይወት ታጥቀህ ተነሥ፥
ለውነት ታገል በርትተህ።
የሱስ ምሳሌ ሆኖዋል
ብርቱ ቆራጥም ነበር
ታማኝ ሁንለት ለጌታ
ያለህን ለርሱ አስረክብ።
ያለህን ለጌታ አስረክብ
የወጣት ጉልበትህን፥
የደኅንነትን ትጥቅ ልበስ፥
ለውነት ታገል በርትተህ።
፪፡ ያለህን ለጌታ አስረክብ
ዋናውን ቦታ ስጠው
በቅድሚያ እርሱን አገልግል፤
ከልብህ ለርሱ ሥራ፥
ብትሰጥ ይጨመርልሃል
አምላክ ልጁን ሰጥቶሃል፥
በውነት ልታገለግለው
ያለህን ለርሱ አስረክብ።
ያለህን . . .።
፫፡ ያለህን ለጌታ አስረክብ
የፍቅሩ ውለታ ነው
ራሱን ላንተ አሳለፈ
ክብሩንም ትቶ መጣ።
ሳይሳሳ ሕይወቱን ሰጠ
ከኃጢአት ሊያድንህ፥
ከልብህ እርሱን አምልከው
ያለህን ለርሱ አስረክብ።
ያለህን . . .።