መዝሙር 293 የሱስ ባንተ ድኜ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የሱስ ባንተ ድኜ
ገንዘብህም ሆኜ
ባንተ ጻድቅ ነኝ
ግን በዓለም ነገር
ልቤ እንዳይታሰር
አንተ ጠብቀኝ።
፪፡ ክፉው ጠላቴ
ወጥመድ ለጥፋቴ
ዘርግቶብኛል።
በኔ ሲቀናብኝ
ሀብቴንም ሊነጥቅብኝ
ዘወትር ያደፍጣል።
፫፡ ስለዚህ ወደኛ
አንተ ቸር እረኛ
ናና ጠብቀን።
ታናሽ መንጋህንም
ጋርደን አድነንም
ተንከባከበን።