መዝሙር 279 ኮብልላ ነበረች ነፍሴ ከአምላክ መንገድ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ኮብልላ ነበረች ነፍሴ ከአምላክ መንገድ
በጣም የበደልኩኝ ኃጢአተኛ ነበርኩ
ግን አዳኜ ከላይ ፍቅር ሰጠኝ ሰላም
እጁን ዘረጋና አዳነኝ።
ደሙን ለኔ አፍስሶ አዳነኝ
ደሙን ለኔ አፍስሶ አዳነኝ
የማልረባም ብሆን አምላኬን የማላውቅ
እጁን ዘረጋና አዳነኝ።
፪፡ ተስፋ ቢስ ነበርኩኝ ሊያድነኝ ሲመጣ
ግን እርሱ ነገረኝ ነጻ እንደምወጣ
ከዚያም አነሳና በጸጋው አዳነኝ
እጁን ዘረጋና አወጣኝ።
ደሙን ለኔ አፍስሶ . . .።
፫፡ የማይገለጽ ደስታ ሰላም ከሰጠኸኝ
ጌታ ሆይ ሕይወቴን ላንተ እሰጣለሁኝ
እንግዲህ መድኅኔ ካንተም ጋር አኑረኝ
እጁን ዘረጋና አወጣኝ።
ደሙን ለኔ አፍስሶ . . .።