መዝሙር 237 የኔ ነህ የሱስ ሆይ እወድሃለሁ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የኔ ነህ የሱስ ሆይ እወድሃለሁ
ስላንተ ያለምን ደስታ ትቻለሁ።
ቅዱስ አምላኬ ሆይ፥
ሁን መድኃኒቴ፤
እጅግ የምወድህ ቸሩ ጌታዬ።
፪፡ እኔ የምወድህ ብትወደኝ ነው
ነፃነቴን በክቡር ደምህ ገዛኸው።
ስላደረግህልኝ ተመስገን ጌታዬ፥
እጅግ የምወድህ ቸሩ ወዳጄ።
፫፡ በሕይወት በሞትም እወድሃለሁ
ትንፋሽ ካለኝ ደግሞ እወድሳለሁ።
በጠራኸኝ ቀንም እላለሁ አምላኬ፥
እጅግ የምወድህ ቸሩ ጌታዬ።
፬፡ በከበረ ስፍራ በማያልቅ ደስታ
ላመሰግንህ ነው የነፍሴን ጌታ።
ዘውድ ደፍቼ ደግሞ ላይህ ነው የሱሴ፥
እጅግ የምድህ ቸሩ ጌታዬ።