Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 70 አርነት ወጣን ነጻም ሆነናል የዘፈን ግጥሞች
፩፡ አርነት ወጣን ነጻም ሆነናል፤
ጌታችን የሱስ ተበዥቶናል።
ሲኦልን ሻረ ሕዝቡን አዳነ፤
በገርነት እንቀበለው።
፪፡ ትልቅ ደስታ ነው አርነት መውጣት
በክርስቶስ ነፃነትን ማግኘት፤
ለየሱስ መሆን እርሱንም ማመን
የዘለዓለም ሕይወት ማግኘት።
፫፡ የሱስ ሆይ ላንተ ይሁን ምስጋና
ስለፈሰሰው ቅዱስ ደምህ።
ሸክማችን ቀረ ኀዘንም ጠፋ፤
ንብረታችንም ተሻሻለ።
፬፡ ወደ ቤታችን ወደ አምላካችን
እንሄዳለን እንደ ተስፋው።
ያረጀ ሥጋ እንተዋለን
አዲስ ሕይወት እንለብሳለን።