Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 287 ወደ መቅደስ ተራሮች የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ወደ መቅደስ ተራሮች
ዓይኔን አነሣለሁ
ረድኤት ከጌታ አለች
በፍቅሩ አምናለሁ።
ረድኤት ትመጣለች
ሁሉን ከፈጠረ
ትሰማለች ጸሎቴ
በሕያው አምላኬ።
፪፡ እግሬን ለመናወጥ
አምላኬ አይሰጥም
ጠባቂዬ በእርግጥ
ከቶ አይደክምም።
እርሱ ጸጋውን ሰጠኝ
ከኃጢአት እንድድን
ዘወትር ይቆምልኛል
እስክደርስ ወደ ላይ።
፫፡ አምላክ ነፍሴን ከክፉ
ዘወትር ይጠብቃል
የሚደርስብኝ ሁሉ
ጥቅም ይሆነኛል።
ይባርካል መግባቴን
መውጣቴን ያቀናል።
በአምላክ የሚማጠን
ምሕረትን ያገኛል።