Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 270 የመንፈሴን ጉድለት የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የመንፈሴን ጉድለት
አምላክ ሆይ አስረዳኝ።
ጸጋን እንዳገኝ
ያን ጤናማ ጭንቀት።
የመንፈስ ደኅንነት
አትውሰድብኝ።
፪፡ ያለም መንገደኛ
እንደ ችግረኛ
ራሱን በመካድ
ወደ ክርስቶስ ጸጋ
በምነት እንዲጠጋ
ነው ያምላክ ፈቃድ።
፫፡ ለመዳንህ ተግተህ
በምግባር ተመክተህ።
ጻድቅ ከመባል
እንዳንድ ምስኪን ርኵስ
ብትድን በየሱስ
ይህ ይሻልሃል።
፬፡ የሱስ ያዳናቸው
ምስኪኖች ቀራጮች
አመሰገኑት።
ፈሪሳውያን ግን
እንደ ዓለም መድኅን
አልተቀበሉትም።
፭፡ ጽድቅን በመፈለግ
ተስፋዬን ከማድረግ
አምላክ አድነኝ።
ነገር ግን ኦ የሱስ
ጻድቅና ቅዱስ
እንድሆን እርዳኝ።