Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 243 ኀዘን ወይም ደስታ የሚደርሰነ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ኀዘን ወይም ደስታ የሚደርሰነ
ማን ያውቃል?
ጌታ የሱስ ከእኛ ጋራ ከሆነ
ይበቃናል።
በርኅሩኅ ድምፁ ያርፋል ነፍሳችን
ሰላምና ደስታ በሕይወት አለን።
፪፡ ችግራችን ሁሉ ባንተ ስናምን
ይጠፋል፤
ኃይል በድካም ረድኤት በመከራ
ይሆነናል።
ጭንቀት የሞላው ይህ ምድራዊ ሕይወት
ከአንተ ዘንድ ይሆነናል ገነት።
፫፡ በምድር ላይ ኃጢአት ስለ በዛ ይጨልማል
አንተን ስለ ከዳን ፍትህም ከእኛ ይሰወራል
በምሕረትህ እንማጠናለን
በርኅሩህ እቅፍህ ውስጥ አሳርፈን።
፬፡ ቸሩ የሱስ ሆይ በሕይወት በሞት ረጃችን ሁን
ደግፈን ከክፋት ስንጋጠም ስጠን ድሉን።
ሁን ከኛ ቀናችን ሲመሽብን
ብርሃን ሁንልን ደስታንም ስጠን።