Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 218 ና ጌታ የሱስ የክብር ንጉሥ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ና ጌታ የሱስ የክብር ንጉሥ
ልቤን አሙቀው በውስጡ ነግሥ።
ጣዖትን አርቀህ ኃጢአቴን ደምስስ
ና ጌታ የሱስ።
፪፡ ቸር ወዳጄ ሆይ፥ በጸጋህ ጐብኘኝ
ረጂ አንተ ነህ ደስም አሰኘኝ።
ምሕረትህን ከጅህ ልቀበል አሁን
ና ጌታ የሱስ።
፫፡ በኃዘን ሁሉ ና ና አጽናናኝ
ፍርሃት ሲይዘኝ ጭንቀት ሲሰማኝ።
ጌታ አድነኝ መጠጊያ ሁነኝ
ና ጌታ የሱስ።
፬፡ የሱስ ሲመጣ በታላቅ ግርማ
ክብር ይሰጣል ልቡ ለነፃ።
በቶሎ ይምጣ ይቅረብ ወደኛ
ና ጌታ የሱስ።