Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 217 ላምላክ ሥራ ደካማ ነኝ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ላምላክ ሥራ ደካማ ነኝ
ኃይልና ብርታት ሁነኝ።
በድካሜ ኃይልህ ይታይ
ሥራዬ ክብርህን ያሳይ።
፪፡ በልቤ ፍጠር ቅን እምነት
ፍቅርን አሳድርበት።
ጭንቀትና ሞት በሞላበት
ላገልግልህ በሐሴት።
፫፡ ዘወትር ምራኝ ባንተ ሥምረት
ደግፈኝ ዕለት ዕለት።
እሰከ ዘላለም ያንተ ነኝ
ማንም ካንተ አይለየኝ።