Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 149 ኦ የሱስ ጌታዬ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ኦ የሱስ ጌታዬ
አመሰግንሃለሁ።
ቅዱስ እራትህን
ሰጥተኸኛል አሁን።
በከበረ ደምህ
ነፍሴን ስላረካህ።
ሰላምና ደስታ
በእርሱ አገኘሁ።
፪፡ የኃጢአቴን ሸክም
ከኔ አስወገድህልኝ።
ዘላለማዊ ጽድቅ
ፍጹም አጎናጸፍኸኝ።
በጸጋህ የእምነት ኃይል
ካንተ ተቀበልሁ።
በጽኑ ሕመምህ
ዕረፍት አገኘሁ።
፫፡ ታዳጊ ጌታ ሆይ
እኔ ያንተ ገንዘብ ነኝ።
ከኃያሉ እጅህ
ከቶ ማንም አይነጥቀኝም።
በሕይወቴ ዘመን
ከአንተ አትለይ፤
በቅዱስ መንፈስህ
ዘወትር እርዳኝ አሜን።