መዝሙር 563 በሰማያት በሰማያት የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ በሰማያት በሰማያት
በአለበት ጌታ
ይታደላሉ ቅዱሳን
ብፅዕናና ደስታ፡፡
ያዩታል ጌታን ፊት ለፊት
ይዘምራሉ ቀን ሌሊት
ለአምላክ ጸባኦት
፪፡ በሰማያት በሰማያት
እንዴት ያለ ብርሃን፡፡
ከቀን ፀሐይ ከጸዳሉ
ይደምቃል ያምላክ ፊት፡፡
ያ ዘላለማዊ ብርሃን
የሚያበራ በሰማያት
ነው አምላክ ጸባኦት፡፡
፫፡ በሰማያት በሰማያት
ያምላካችን ጭፍራ
ከብፁዓን ቅዱሳን ጋር
ይታደላል ደስታ፡፡
ነፍሴ እጅግ ደስ ይበልሽ
ብፅዕና ስለሚቆይሽ
ካምላክ ጸባኦት ዘንድ፡፡
፬፡ በሰማያት በሰማያት
ጭንቀትና ሥቃይ
ኀዘን መከራና ሞትም
ከቶ የለም በላይ፡፡
ይሰጣል ደስታ ሕይወትም
ይታደላል ክብር ሰላም
ካምላክ ጸባኦት ዘንድ፡፡
፭፡ በሰማያት በሰማያት
ግሩም ድንቅ ብፅዕና
ሰዎች ያላዩትን ደስታ
ይሰጠናል ጌታ፡፡
መዋቲ ልብ ያላሰበው
መዋቲ ድምፅ ያልዘመረው
ኦ አምላክ ጸባኦት፡፡
፮፡ በሰማያት በሰማያት
ለቅድስት ሥላሴ
ለአብ ለወልድ ለመንፈስም
ይሰጣል ውዳሴ፡፡
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ
ሲሰግዱለት ጭፍሮቹ
በአምላክ ጸባኦት።
፯፡ ኦ አብ ኦ ወልድ ኦ መንፈስም
ላመስግንህ እርዳኝ
ወደ ሰማያዊ ቤትህ
በፀጋህ አድርሰኝ፡፡
አሁንም በምነት ጠብቀኝ
አንድ ቀን የሕይወት ዘውድ ስጠኝ
ኦ አምላክ ጸባኦት፡፡