መዝሙር 528 ወደ ቅዱሱ ቁስሉ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ወደ ቅዱሱ ቁስሉ
ነፍሴ ሆይ ቅረቢ።
በሥቃዩና ሞቱ፥
ሕይወት ሆነ ላንቺ።
በሕይወት ልትኖሪ፥
በደሙ አዳነሽ።
ዕዳሽን ሁሉ ከፍሎ፥
በምሕረት ከለለሽ።
፪፡ ከቶ የዓለም ጥሪት
ሊያድነን ከጥፋት
አልቻለም በአምላክ ፊት።
ስለዚህ ጌታችን፥
ቅዱሱ የአምላክ ልጅ፥
አስታራቂ ሆነን።
ከጠላታችንም እጅ
በሞቱ አዳነን።
፫፡ በየሱስ ከአመንሁ
በርግጥ እድናለሁ
ጽድቁን ከተቀበልሁ፥
ሕያው እሆናለሁ።
ንጹሕ ደሙን አፍስሶ፥
ያምላክ ልጅ ሞተልኝ።
ኃጢአቴን ደምስሶ፥
ሕይወቴን ዋጀልኝ።
፬፡ ደሙ ስላጸደቀኝ
አብ ይቀበለኛል።
የልጁ ሙሽራ ነኝ፤
በርሱ ደስ ይለኛል።
ከኔ ጋር ተባበረ፥
ያለም ፍትወት ይጥፋ።
የሱስ በኔ ካደረ
የርሱ ነኝ በተስፋ።
፭፡ ቁስሎቹ በሰማይ
ብሩካን ደጆች ናቸው።
ላማኞች ሁሉ በላይ፥
መግቢያ በር አላቸው።
ለሚታመነው ድሀ
የወልድ ደም ፈሰሰ።
ቅዱስ የሕይወት ውኃ፥
ርኩሰቱን ፈወሰ።
፮፡ ወደ ቅዱስ ቁስሉ
ነፍሴ ሆይ ቅረቢ።
ሕየወትሽን በሙሉ፥
ከርሱ አትራቂ።
በዚህ ቅዱስ አምባ ላይ፥
ሰላም ታገኛሽ።
ከዘላለም ሞት ሥቃይ
በርሱ ትድኛለሽ።