መዝሙር 51 ሕይወቴን ለወጥሁልህ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ሕይወቴን ለወጥሁልህ
ልገዛ ነፍስህን፥
ሰማይን ልከፍትልህ፥
ልሰጥህ ርስትህን።
ትድን ዘንድ ደሜ ፈሶአል፥
ምን መልሰህልኛል?
ትድን ዘንድ ደሜ ፈሶአል፥
ምን መልሰህልኛል?
፪፡ ዙፋኔን ያባቴን ቤት
ትቼው ያንን ብርሃን፥
ባለም ጨለማና ሌት፥
በዚች ምድር ኅዘን።
ስላንተ ነው ላንተ ብዬ፥
ምን ሆነ ዋጋዬ?
ስላንተ ነው ላንተ ብዬ፥
ምን ሆነ ዋጋዬ?
፫፡ ስላንተ ብፅዕና
እኔ ተሠቃየሁ፥
ስላንተም ብልጥግና፥
እኔ ደኸየሁ።
ስላንተ ሁሉንም ትቼ፥
ምን ሆነ ዋጋዬ?
ስላንተ ሁሉንም ትቼ፥
ምን ሆነ ዋጋዬ?
፬፡ ከኃጢአት ከሞትም
ላድንህ መጣሁ፥
በልብህ ውስጥ ልኖርም፥
ደጅህን መታሁ።
ስጠኝ ልጄ ሆይ ምኞቴን፥
ልብህን ደመወዜን።
ስጠኝ ልጄ ሆይ ምኞቴን፥
ልብህን ደመወዜን።