መዝሙር 508 ጌታ ኢየሱስ ሆይ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ጌታ ኢየሱስ ሆይ የዓለም መድኅን
ከአብ ዘንድ የተላክህልን
በቃልና በመንፈስ ጸጋ፥
ያምላክ ልጆች ያደረግኸን።
፪፡ የጠፋነውን የሚፈልገን
ቸር እረኛ ኢየሱስ ነው።
በይቅርታ የሚቀበለን
አማላጅ ጻድቅ ፈራጅ ነው።
፫፡ እንከተል እረኛችንን
በደሙ ኃይል የዋጀንን
በዘላለማዊ ድንቅ ፍቅሩ
የሚያኖረን በገነቱ።
፬፡ አዎን አሜን ለዚህ ቸር ጌታ
የሱስ ክርስቶስ የኛ አለኝታ
እንስገድለት በዕልልታ
እንዘምር በደስታ።