መዝሙር 475 ግሩም ነው የየሱስ ፍቅር የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ግሩም ነው የየሱስ ፍቅር
ኃጢአቴን ሸፈነው።
ግሩም ነው የየሱስ ፍቅር፥
ፍጹም ነጻ አወጣኝ።
በየሱስ ደም ታጥቤአለሁ፥
ፈቃዱንም አደርጋለሁ።
ለዘላለም እዘምራለሁ፥
ግሩም ነው የየሱስ ፍቅር።
ግሩም ነው ግሩም ነው
ግሩም ፍቅር
ግሩም ነው የየሱስ ፍቅር።
፪፡ ግሩም ነው የየሱስ ፍቅር
ፈልጎ ያገኘኝ።
ግሩም ነው የየሱስ ፍቅር፥
ልጁ አደረገኝ።
ኃጢአቴንም ይቅር ብሎ፥
ለዘላለም አዳነኝ።
በኃይሉም ጸንቶ አቆመኝ፥
ግሩም ነው የየሱስ ፍቅር።
ግሩም ነው . . .።
፫፡ ግሩም ነው የየሱስ ፍቅር
በሰማይ ቤት አለኝ።
ግሩም ነው የየሱስ ፍቅር፥
በደሙ የሠራው።
በተቀደሰ ማደሪያው፥
ሥፍራ አዘጋጅቶልኛል።
ከልባችን እንመነው፥
ግሩም ነው የየሱስ ፍቅር።
ግሩም ነው . . .።