መዝሙር 469 ቸሩ መድኃኒቴ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ቸሩ መድኃኒቴ
የመጣህ በፍቅርህ።
ወደ ዓለም ውርደት፥
ከጥንታዊ ክብርህ።
፪፡ ሕይወቴን ለማዳን
ተሸክመህ ቅጣት፤
ፍቅርህ አደረሰህ፥
ለሥቃይና ሞት።
፫፡ አቤቱ ፍቅርህን
ግለጠው በላዬ፣
ብርሃንህን ስጠኝ
በጨለመ ልቤ።
፬፡ በጨለማ ዓለም
ለታሰረ ነፍሱ፣
የጸጋን አርነት፥
ግለጥለት ለእርሱ።