መዝሙር 446 ምሕረቱ አያልቅምና የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
ምሕረቱ አያልቅምና
ለዘላለም ቸር ነውና።
የማዳን ኃይሉን ላሳየን፥
በክንዱ ለሚጐበኘን
መልካሙን መዓዛ በምስጋና
አቅርቡለት፥
በዕልልታም ስገዱለት።
፩፡ ከባቢሎን ወንዞች ማዶ አዝነን ተቀምጠን
ጸዮንን ባሰብናት ጊዜ እጅግ አለቀስን።
የመጽናናት አምላክ ከላይ ግን ያየናል
እንባችንን ጠርጎ ስብራታችንን ይጠግልናል።
ምሕረቱ . . .።
፪፡ የችግረኞችን ጩኸት ሰምቶ አይጨክንም
ምርጦቹን ከልቡ በፍጹም አያስጨንቅም።
የሚያጽናናን አምላክ ከላይ ግን ያየናል፤
እንባችንን ጠርጎ፥
ስብራታችንን ይጠግንልናል።
ምሕረቱ . . .።
፫፡ በሥጋቸው የገነኑ ፈጽመው ሲወድቁ
እግዚአብሔርን በመታመን የሚጠባበቁ።
በእንባቸውን ፍሬ እያሸበረቁ፥
በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ፥
ይከብራሉ እንደ እንቁ።
ምሕረቱ . . .።
፬፡ ለእኛ መጠጊያችን ጌታ እግዚአብሔራችን ነው
በምንም አንፈራም እርሱ ኃይላቸን ነው።
ከጠላት አሸክላ ስሙ ይጠብቀናል፥
ላሞራም ሳይሰጠን፥
በክንፎቹ አዝሎ ቤቱ ያገባናል።
ምሕረቱ . . .።