መዝሙር 434 አቀርባለሁ አቀርባለሁ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ አቀርባለሁ አቀርባለሁ
ጌታን ለማየት እሻለሁ።
ነፍሴ ጌታዋን ናፈቀች፥
መድኃኒትዋንም ፈለገች፥
በፊቱ እንድትቆም።
፪፡ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ጌታ
ብለው ሲዘምሩ ብፁዓን
ለመብረር ክን – ፍ ቢኖረኝ፥
በርሬ ቶሎ በሄድኩኝ፥
በዚያ ቤት ለመገኘት።
፫፡ ታላቅ ደስታ ታላቅ ደስታ
በዚያ በታላቅ አዳራሽ።
ከቅዱሳን ጋር መኖር
ማ – ንም በማይገምተው፥
በታላቁ ያምላክ ቤት።
፬፡ እርዳን ጌታ እርዳን ጌታ
ወደ ሰማይ አድርሰነ።
ከሕይወት ምንጭ አጠጣነ፥
አዲስ መዝሙር ለመዘመር፥
ጌታ የሱስ ሆይ አብቃን።