መዝሙር 428 ወደከበረው አገር በላይ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ወደከበረው አገር በላይ
እናያለን በሃይማኖት ዓይን።
ጥሩ ቤት አለን በሰማይ፥
የተዘጋጀ በየሱስ ቤት።
ቅርብ ነው ጊዜው፥
ልንገናኝ በሰማይ አገር፤
ቅርብ ነው ጊዜው፥
ልንገናኝ በሰማይ አገር።
፪፡ ስንፈታ ከሞት እሥራት
እንኖራለን በዚያ ድንቅ አገር።
ከጌታችንም ጋር በአርያም፥
ልንዘምር ነው የብፁዓን መዝሙር።
ቅርብ ነው . . .።
፫፡ አምላካችን የፍቅር አባት
ስለገለጥህልን ፍቅርህን።
ስለ ሰጠኸንም ጸጋህን፥
እናመስግንህ ዕለት ዕለት።
ቅርብ ነው . . .።