መዝሙር 366 የጠፉትን ደግሞ ለመሻት የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የጠፉትን ደግሞ ለመሻት
በደግነቱ እየጠራ፤
ኑ እያለ መልእክቱ ይጠራል፥
የጌታ ቃል ዛሬ ይሰማል።
ርቆ ሂዶ ወደ ተራራው።
ኮብላዩን ሊያመጣ፤
ጌታ የሱስ መድኃኒታችን፥
ለእኛ ብሎ የተሰዋው።
፪፡ የይቅርታ መንገደኛ ሁኜ
ልጓዝ ከርሱ ጋር በየዕለቱ፤
ለጠፉት መንገዱን እያሳየሁ፥
የደከሙትን እያጽናናለሁ።
ርቆ ሂዶ . . .።
፫፡ የጠፉትን ወደ ኢየሱስ ማምጣት
የደከሙትን ያዘኑትን፤
ከኢየሱስ ጋር እንዲራመዱ፥
የሕይወት መንገዱን እንዲያውቁ።
ርቆ ሂዶ . . .።