መዝሙር 362 የሱስ ለስለስ ባለ ድምፅ ይጠራሃል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የሱስ ለስለስ ባለ ድምፅ ይጠራሃል
እኔና አንተን ይጠራል።
እየው በሩ ላይ ቆሞ ይቆይሃል፥
እኔና አንተን ይቆያል።
ግቡ ግቡ ደካሞች ሁሉ ግቡ፥
የሱስ ወደ ቤቱ ይጠራችኋል፥
ኃጢአተኞች ኑ አሁን።
፪፡ ለምን አትሄድም የሱስ ሲለምን
እኔና አንተን ሲለምን።
ለምንስ ምሕረቱን አታስበውም፥
እኔና አንተን ሲምረን።
ግቡ ግቡ . . .።
፫፡ ጊዜውና ደቂቃው ያልፍብናል
ከኔና ካንተ ያልፋል።
ሞትም ጥላውን በኛ ላይ ይጥላል፥
በእኔና ባንተ ላይ።
ግቡ ግቡ . . .።
፬፡ ባስደናቂው ፍቅሩ ተስፋ ሰጥቶናል
ለኔና ላንተ ሰጥቷል።
ምንም ብንበድለው ይቅር ይለናል፥
እኔና አንተን ይምራል።
ግቡ ግቡ . . .።