መዝሙር 360 ኑ የአምላክ ወዳጆች ደስታችን ይገለጥ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ኑ የአምላክ ወዳጆች ደስታችን ይገለጥ
በድንቅ ዜማ እንዘምር፥
ወንጌሉን እናብስር፥
በዙፋኑ ዙሪያ በዙፋኑ ዙሪያ።
እንጓዝ ወደ ላይ ወደ ውቢትዋ ከተማ፥
እንገሥግስ ወደ አምላካችን፥
ወደ ቅድስት ኢየሩሳሌም።
፪፡ በጽዮን ተራራ ከቅዱሳን ጋራ
በሰማያዊ አዳራሽ ብርሃኑ በሚያንጸባርቅ፥
በወርቃማው መንገድ
በወርቃማው መንገድ።
እንጓዝ ወደ ላይ . . .።
፫፡ ማኅሌታችን ይድመቅ እንባ ሁሉ ይድረቅ
አማኑኤል ከኛ ጋር ነው
የማይክድ አምላካችን ነው፥
በመልካምዋ አገር በመልካምዋ አገር።
እንጓዝ ወደ ላይ . . .።