መዝሙር 357 የሱስ ወደ እኔ ኑ ይለናል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የሱስ ወደ እኔ ኑ ይለናል፤
ሰምቶ የሚመጣውን ይቀበላል።
ማንንም ወደ ውጭ እንደማይጥል
ቃሉ ይመሰክራል።
ወደ እኔ ኑ ሲል ይጠራናል፤
ድምፁ ለሁላችንም ይሰማናል።
ጥፉን ልጅ አባቱ ተመለስ ይለዋል፤
እኛንም ይጠራናል።
፪፡ መንገድ እውነት ሕይወት የሱስ ሆኖአል፤
የሰማይም ደጅ በእርሱ ተከፍቶአል።
አንተም ለመግባት እድል ተሰጥቶሃል፤
ላንተም ተከፍቶልሃል።
ወደ እኔ ኑ . . ..።
፫፡ የሚመጣ ሁሉ ጸጋ ያገኛል
የየሱስን ትሩፋት ይቀበላል።
ከሞት ወደ ሕይወትም ይሻገራል
በመድኃኒታችን ቃል።
ወደ እኔ ኑ . . .።