መዝሙር 353 ኑ ደካሞች ሁላችሁ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ኑ ደካሞች ሁላችሁ
ወደ ሙሉ ሰላም።
ሕይወት የሚሰጣችሁ
ወሮታ አይሻም።
ግሩም ነው ያምላክ ቸርነት
የፍቅሩ ትሩፋት።
ለእኛ የሚሰጠን
በጸጋው ብዛት።
፪፡ የሱስን እየው ቶሎ
አሁን ይጠራሃል።
ብትዘገይስ ፈጥኖ
ዘመንህ ያልፋል።
ፍቅሩን አትናቀው፤
አሁን ተቀበለው።
ገዝቶሃልና ለርሱ
ልብህን ስጠው።
፫፡ ቸኩል ወደርሱ አሁን፥
አንተን ይጠብቃል።
የተዘጋጀ ክብሩን
ያቀርብልሃል።
ፍጹም ምስኪን መሆንህን
እርሱ በጣም ያውቃል።
የሚያስፈልግህን፥
ወዶ ይሰጣል።