መዝሙር 32 ጽዮን ሆይ፥ መሢህሽ ይመጣል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ጽዮን ሆይ፥ መሢህሽ ይመጣል
ነቢያት የተነበዩለት
የሰላም ዘንባባ ዘርግተሽ
እንደሙሽራ ተዘጋጂ።
ደስ ይበልሽ
ለጌታ ዕልልታን አቅርቢ
ደስ ይበልሽ
ለአምላክ ስብሐት አቅርቢ።
፪፡ ከነበረው ደስታና ክበር
የወርቅ ዙፋኑን ትቶ
የሰማይን ክብር ሠውቶ
ይመጣል ትሕትናን ለብሶ።
ደስ ይበልሽ . . . .።
፫፡ የኃጢአት መሥዋዕት ይሆናል
ለሰው ሲል ወደ ሲኦል ወርዶ
የሞትን ቀንበር አሸንፎ
አማኞችን ድል አጐናጽፎ።
ደስ ይበልሽ . . .።
፬፡ ኅዘንተኛውን ያጽናናል
የሕይወት ብርሃን ያለብሳል፥
ክፉውን ሁሉ አሸንፎ
በግርማና ክብር ይነግሣል።
ደስ ይበልሽ . . .።