መዝሙር 247 እዘምራለሁ ላዳኜ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ እዘምራለሁ ላዳኜ
ላስደናቂው ፍቀሩ ስል
ተሰቃየልኝ በመስቀል
ከመርገም እኔን ሊያድን።
ዘምሩ ላዳኜ ክብር
በደሙ እኔን ገዛኝ
በመስቀሉ ይቅር አለኝ
ዕዳዬን ከፈለልኝ።
፪፡ ድንቁን ታሪክ እነግራለሁ
ከጥፋቴ እንዳዳነኝ
ሰፊ በሆነው ምሕረቱ
በትርፍ ሁሉን ለሰጠኝ።
ዘምሩ ላዳኜ . . .።
፫፡ ውድ አዳኜን ላመስግነው
ድል ነሺ ኃይሉን ልንገር
በሞትና በሲኦል ላይ
አሸናፊ ላረገኝ።
ዘምሩ ላዳኜ . . .።
፬፡ እዘምራለሁ ላዳኜ
ለሰማያዊ ፍቅሩ
ከሞት ሕይወትን አሳየኝ
በርሱም ያምላክ ልጅ ሆንሁኝ።
ዘምሩ ላዳኜ . . .።