መዝሙር 225 ልጆቹን ለማከማቸት የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ልጆቹን ለማከማቸት
ጌታችን ሲመለስ፥
ጥሩ ስንዴውን ለመክተት
በክብሩ ሲገለጥ።
ያን ጊዜ ያምላክ ልጆች
በክብሩ ይደምቃሉ፥
ያበራሉም እንደ ዕንቈች
በግሩም አክሊሉ።
፪፡ የሱስም የዋጀውን ነፍስ
በደሙ የነጻ።
ቅዱስ መንጋውን ለመሰበሰብ፥
ወደኛ ሲመጣ።
ያን ጊዜ . . .።
፫፡ የሱስንም የሚወዱ
ታናናሾች ልጆች
ይሆናሉ ጌጥ ለዘውዱ
የየሱስ ወዳጆች
ያን ጊዜ . . .።