መዝሙር 216 ከዚህ ምድር ወደ ሰማይ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ከዚህ ምድር ወደ ሰማይ
ዓይኔ በእምባ ናፈቀ።
ከዚህ ዓለም ወደ ሳሌም
ነፍሴም ደግሞ ቃተተች
ችግሬ ይወገዳል
መንገዴም ብሩህ ይሆናል።
፪፡ ቀድመውን ያለፉት ሁሉ
ለምጽአት ተሰብስበው
ነጭ ልብሳቸውንም ለብሰው
በክብር ሊቀበሉት
ነፍሴ ሆይ፥ ተዘጋጂ
ጌታሽን ተቀበይ።
፫፡ ምሕረቱ እግጅ ሰፊ ነው
በደሙ ለተዋጀን
ከብፁዓን ጋር በኅብረት
ንጉሡን ስንቀበል
የኛ ትምክህት ይጠፋል
ጸጋው ይበዛልናል።
፬፡ ኢየሱስ ሙሽራይቱን
ግርማ አጐናጸፋት
በዚያ አገር ኀዘን ችግር
ፈጽሞ ሳያገኛት
ላጭር ጊዜ ብሠቃይ
ዘውድ ይቆየኛል በላይ።
፭፡ መድኃኒቴ ሆይ ጠብቀኝ
ሁልጊዜ አትለየኝ
በቸርነትህ ጠብቀህ
እንድታዘዝህ አጽናኝ
ነፍሴን በቡሩክ ሰንበት
ወደ መንግሥትህ አግባት።