መዝሙር 129 ተነሥቼ ወደ አባቴ ልሂድ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ተነስቼ ወደ አባቴ ልሂድ
በቅን ሕሊና ኑዛዜን ላድርግ።
እንዲህ ልበል፦ አባቴ ሆይ ተውልኝ
በሰማይና በፊትህ በደልሁኝ።
፪፡ መሐሪ አምላኬ ሆይ፥ ይቅር በለኝ
በጸጋህ ኃጢአቴን ደምስስልኝ
ሰላም ስጠኝ ደስታን አውርድልኝ
ተቀበለኝ ስል እጮሃለሁኝ።
፫፡ ኃጢአቴ እንደበዛ ቢሰማኝም
የአምላኬ ምሕረት ግን ይበልጣል።
ወደ አባቴ ተመልሼ ስመጣ
በፍቅር አቅፎ ይቀበለኛል።
፬፡ ተነሥቼ ወዳባቴ ልመለስ
ልማጠን ነኝ በአባትነቱ።
እኔ የጠፋሁ ወዳምላክ ስመለስ
በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል።