Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 94 ከበደሌ ከኃጢአቴ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ከበደሌ ከኃጢአቴ
ወዴት ልሽሽ ኦ አምላኬ?
በጣም እጨነቃለሁ
ሕግህን ሁሉ አፍርሼ
ከአንተ ርቄ ሸሽቼ
ፍርድህን እፈራለሁ።
ነፍሴን ኀዘን ደቆሰው
ልቤንም ጸጸት ሰበረው።
ጌታዬ ሆይ ራራልኝ
ምሕረት አድርግልኝ።
፪፡ አምላክ ሆይ ቃልህ ሕይወት ነው፤
ለነፍሴ በጣም ጣፋጭ ነው፤
ልቀበለውም እሻለሁ።
የሱስ ወዳለም መጥቶአል፤
ኃጢአቴን ደምስሶልኛል፤
እኔ በርሱ ድኛለሁ።
ወንበዴውን የተቀበለው፥
በገነትም ያሳረፈው፥
እኔን እንደሚቀበል፥
ቅዱስ ወንጌል ነግሮኛል።
፫፡ ይሱስ ክርስቶስ ይዳዊት ልጅ፥
ልቤን ከእጆቼ ጋራ
ወዳንተ አነሣለሁ።
እኔን የረከስሁ አጥራኝ፤
ከኃጢአት እድፍ አንፃኝ፤
በአንተ አምናለሁ።
እንደ ጠፋው በግ ነበርሁኝ፥
በአንተ ግን ተገኘሁኝ፤
አንተ የምትራራ
አኑረኝ ካንተ ጋራ።