Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 90 ጽዮን ተነሺና አብሪ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ጽዮን ተነሺና አብሪ
ብርሃንሽ መጥቶአል።
አምላክ ከሰጠሽ ስጦታ
ለዓለም አካፍይ።
ያምላክ ክብር ተገልጦልሻል
አመስግኚው በደስታ
ዘምሪ ሃሌ ሉያ።
፪፡ ኢትዮጵያ ብርሃንሽ
እንዳይጠፋ ጠብቂ፥
የጸጋ ቀን ገና ሳለሽ
ሰላምሽን አስቢ።
ባንቺ እውነት ሰላም ይልማ፥
የአምላክ መንግሥት ይስፋ፥
ጽድቅ በአገሩ ይግዛ።
፫፡ በተራራ የተሠራ
ቤት ከሩቅ እንደሚታይ፥
የእውነት ፍሬ እናፍራ።
ባምላክ ቃል እንመራ።
ጨው ለምድር፥ ብርሃን ላለም
ሆነን ሕዝብን እንጥቀም
በትጋት ሳንለግም።