Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 87 ኦ ቅዱስ አባት የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ኦ ቅዱስ አባት
በጸጋህ ቅረበን
ከቅዱስህ ቃልህ ዞትር መግበን
ልመናችንን ስለ ፍቅርህ ስማን
በኃይልህ እርዳን።
፪፡ ኦ የሞትህልን
ከእኛ ጋራ ሁን
ከዓለም ጭንቀት በጸጋህ አድነን
አበረታታን ደክመን ስንጣምን
ኃይልህን ስጠን።
፫፡ ኦ መንፈስ ቅዱስ
እውነት አሳየን
ሁልጊዜ በቀናው መድገን ምራን
በቅድስናህ ቀድስ ሁላችንን
ኃይልህ ያበርታን።