Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 63 በመቃብር ተኛ የዓለም መድኅን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ በመቃብር ተኛ የዓለም መድኅን፥
ሕያው ሆኖ ለኛ ተነሣልን።
ከመቃብር ተነሣ፥
ጠላራችንን ድል ነሥቶአል፥
ድል ነሥቶአል ለእኛ ነሥቶአል።
ለዘላለም ይነግሥልናል በላይ፥
ተነሣ፥ ተነሣ፥ ሃሌ ሉያ ተነሣ።
፪፡ በከንቱ ጠበቁት ያንን መቃብር፥
በከንቱ አተሙት ያለቱን በር።
ከመቃብር ተነሣ፥
ጠላራችንን ድል ነሥቶአል፥
ድል ነሥቶአል ለእኛ ነሥቶአል።
ለዘላለም ይነግሥልናል በላይ፥
ተነሣ፥ ተነሣ፥ ሃሌ ሉያ ተነሣ።
፫፡ ሞትን አሸነፈ መድኃኒታችን፥
መቃብርን ሻረ አዳኛችን።
ከመቃብር ተነሣ፥
ጠላራችንን ድል ነሥቶአል፥
ድል ነሥቶአል ለእኛ ነሥቶአል።
ለዘላለም ይነግሥልናል በላይ፥
ተነሣ፥ ተነሣ፥ ሃሌ ሉያ ተነሣ።