Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 48 የተሰቀለውን መድኅን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የተሰቀለውን መድኅን
በእምነት ብታይ፥
ይሆንልሃል ሙሉ መዳን።
ና ተመልከት ሲሰቃይ
በመስቀሉ ላይ፥
ሲሽርም የሞትን ሥልጣን።
እይ፥ እይ፥ እይና ዳን
የተሰቀለውን መድኅን
በእምነት ብታይ፥
ይሆንልሃል ሙሉ መዳን።
፪፡ ብትጾም ብትጸልይም
እንባህም ቢፈስ
ያ አይበቃም ለነፍስህ መዳን።
የየሱስ ክርስቶስ ደም ግን
በመስቀል ሲፈስ
ተፈጸመ የኛ መዳን።
እይ፥ . . .።
፫፡ ኃጢአትህ በላይህ
የቀረ ቢሆን፥
የሱስ ክርስቶስ ለም ተቀሠፈ?
የተቀደሰ ስሙ ባይከፍል ዕዳህን
ከጐኑስ ለምን ጐረፈ?
እይ፥ . . .።
፬፡ ትሩፋቱን ተቀበል
በስሙም እመን
የመድኃኒቱን ደም አትናቅ።
በተሠዋ ጊዜ በተሰቀለም ቀን
ከሞት እንዳዳነህ እወቅ።
እይ፥ . . .።