Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 43 የሱስ በመስቀል ሞተልን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የሱስ በመስቀል ሞተልን፤
እንማጠን በፍቅሩ።
እርሱ ከኃጢአታችን
አነጻን በደሙ።
እኛን ወደ አብ ለመሳብ፥
ዐረገልን ወደ ላይ።
በአባቱ ቀኝ ቆመልን፥
በፊቱ ሊያጸድቀን።
፪፡ የሱስ ሆይ በፍቅርህ እርዳን፣
ጸጋህን ለጽድቅ ስጠን።
ልባችንን ለውጥልን፣
ቀድስ ሕይወታችንን።
እንዳንቀር ተኰንነን
በኃጢአታችን ብዛት፥
ሁሉን አንተ ፈጸምህልን፥
አወረስኸንም ሕይወት።