Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 331 የአምላክ ቃል ያሸንፋል የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የአምላክ ቃል ያሸንፋል
የጨለማውን ጭፍራ፤
ክፉ ቅናት፥
ሰይፍ ወይም እሳት
ወንጌሉን አያስቀርም።
፪፡ ባምላክ ትእዛዝ ሰባኮቹ
በመላ ዓለም ወጡ፤
ለማስተማር
ቅዱስ ቃሉን
ሕይወት የሚሰጠውን።
፫፡ ለጨካኞች ላመፀኞች
ወንጌልን ይሰብካሉ፤
በጨለማ
እንዲበራ
ብርሃኑን ያቆማሉ።
፬፡ በዓለሙ ይዘራሉ፤
አምላክ ቃሉን ያለማል፤
በምሕረት ቀን
አንድ ነፍስ ቢድን፥
አምላክን ደስ ያሰኛል።
፭፡ ሕያው ቃሉ ያጸናናል፤
ለተጨነቁ ሁሉ፥
ለአዘኑ፥
ሰላም ላጡ፥
ጽኑ ተስፋ ይሰጣል።
፮፡ ልዑል ንጉሥ በኛ ንገሥ፤
ግዛትህንም አስፋው፥
ድል ያንተ ነው
በዓለሙ፥
ላንተ ይሁን ምስጋና።