Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 320 እኔ መናኝ መንገደኛ ነኝ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ እኔ መናኝ መንገደኛ ነኝ፤
ለጥቂት ጊዜ ብቻ በዚህ ልኑር።
ከአምላክ ሕዝብ ጋር እጓዛለሁኝ፤
ጌታን ተከትዬ እሄዳለሁ፤
ወደዚያ እቸኵላለሁ፤
ለጥቂት ጊዜ ብቻ በዚህ ልኑር።
፪፡ ፋሲካዬን ልብላ በፍጥነት፤
ቅዱስ ደሙ የልቤን መድረክ ይንካ።
ወዳገሬ ልሂድ ከባርነት፤
ከሰይጣን ሥልጣን
ልውጣ አርነት፤
አምላክ ይጠራኛል ለሕይወት፤
በቅዱስ በንጹሕ ደሙ ገዝቶኛል።
፫፡ ወደ ከነዓን ዓይኔ ያያል፤
ለዘላለም፤ ለዘላለም ብሩህ ነው።
በዚህ በጨለማ፥ ሞት ያስፈራል፤
ድካሜ ሁልጊዜ ይጥለኛል።
ወደ አገሬ ዓይኔ ያያል
ለዘላለም፤ ለዘላለም ብሩህ ነው።
፬፡ በዚች ምድር ዕረፍት አይገኝም፤
ወዲያ ነው፥ ወዲያ ነው ምኞቴ
በዚያ ሞት ከቶ አያስፈራኝም፤
ድካም አይሰማኝም ጠላት የለኝም።
ኃጢአት አያስጨንቀኝም።
ወዲያ ነው፥ ወዲያ ነው ምኞቴ።
፭፡ ቸር እረኛዬ አትተወኝ፤
ከኔ ጋራ፥ ከኔ ጋራ ዞትር ሁን።
ወደ ብፅዕና እስክታደርሰኝ፥
ቸር እረኛዬ አትተወኝ።
ከኔ ጋራ፥ ከኔ ጋራ ዘወትር ሁን።