Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 300 አንዳንዴ አምነቴ ሲጠፋ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ አንዳንዴ አምነቴ ሲጠፋ
ብርሃን ሲጨልምብኝ
ያኔ ኢየሱስ ይመጣና
እሰማለሁኝ ሲለኝ
አትፍራ ከአንተ ጋር ነኝ
መሪህም እሆናለሁ።
አትፍራ ስለ ማዕበሉ
እኔ ካንተ ጋር ነኝ።
፪፡ ነፍሴም ስትታወክብኝ
ቀኖቹም ሲረዝሙብኝ
ወደ መድኅኔ አይና
እሰማለሁኝ ሲለኝ
አትፍራ . . .።
፫፡ ፈተናም በጣም ሲበዛ
መንገዴም ሲጠፋብኝ
ዓለሙ ግራ ሲገባኝ
እሰማዋለሁ ሲለኝ
አትፍራ . . .።