Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 279 ያምላክ ሕዝብ የጽዮን ወገን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ያምላክ ሕዝብ የጽዮን ወገን
ወደ ሰማይ ይጓዛል፤
ባለም ባይገኝለት ተገን፥
ካምላክ ዘንድ ተገኝቶአል።
የሱስ ክርስቶስ የገዛቸው፥
በርሱም የሚያምኑ፤
በምድር እንግዶች ናቸው፥
ባለም ተበትነዋል።
፪፡ ባለም ሁሉ ብትጠላ
ከቶ አያስፈራህም፥
የሱስ ልብህን ከሞላ፥
ሌላ አያስፈልግም።
እርሱ ብቻ ሙሉ ተስፋ፥
ሊሆንልህ ይችላል፤
ሌላ ምርኵዝም ቢጠፋ፥
እርሱ ይደግፍሃል።
፫፡ እርሱን ካገኘህ በሙሉ
ሕይወትህ ይበቃሃል።
አምላክ ሁሉ ነው በሁሉ፥
መንጋውን ይጠብቃል።
ድንቢጥም ቤትዋን አገኘች፥
በአምላክ መሠውያ፤
ግሩም አርነት ተገኘ፥
ለተጨነቀው ባርያ።
፬፡ እምነትና ፍቅር ብቻ
አምላክ ፈለገ ከኛ።
ሕግን ሁሉ በመፈጸም፥
ሊድን የሚችል የለም፥
የሚያምን ግን ይድናል።
የሱስ መንፈስህ ይምራን፥
ፍቅርህም ያስፈልገናል፥
የሱስ ሆይ ፍቅርህ ይግዛን።
፭፡ መንፈስህ በዚህ መሠረት
ቅዱስ መቅደስህን ይሥራ፥
እያንዳንዳችንን በእምነት፥
ወደ መስቀልህ ይምራ።
ማኅበርህን ያዳብር፥
ይግለጥለት እውነቱን፥
ሁሉንም ሲያስተባብር፥
በሁሉ አንድ ልብ ይሁን።