Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 276 አንድ ወዳጅ በምሄድበት ሁሉ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ አንድ ወዳጅ በምሄድበት ሁሉ
ከኔ ጋራ ይመላለሳል፤
ላይኔ አይታይም ግን ቅዱስ ቃሉ
ወደ ልቤ ይደርስልኛል።
ያ ወዳጅ ስለኔ ሞቶ ነበር፤
ከመቃብር ግን ተነስቶአል።
እረኛችን ሆኖ፥ በማይነገር
ርኅራኄ ለመንጋው ያስባል።
እረኛችን ሆኖ፥ በማይነገር
ርኅራኄ ለመንጋው ያስባል።
፪፡ ሁልጊዜ የሚያስፈልገኝን፥
ቸር ጌታዬ ያቀርብልኛል።
ልቤንም የሚያቆስለኝን፥
ፈውሶ ረድኤት ይሰጠኛል።
ላጭር ጊዜ እንዲሰወርብኝ፥
እርሱ ራሱ ገልጦ ነግሮኛል።
ግን ተመልሶ ሲገለጥልኝ፥
ደስታና ሰላም ይሆነኛል።
ግን ተመልሶ ሲገለጥልኝ፥
ደስታና ሰላም ይሆነኛል።
፫፡ ድል የነሣ እሙኑ መድኃኒት፥
ቶማስ ሲጠራጠር አሰበው።
እንዲሰጠውም ቅዱስ መጽናናት፥
ቍስሎቹን አመለከተው።
ቶማስ ጌታን አውቆ አዲስ ተስፋ፥
ሙሉ እምነትም ተቀብሎ፥
ጮኸ በማይነገር ቅዱስ ደስታ፥
ገታዬና አምላኬ ብሎ።
ጮኸ በማይነገር ቅዱስ ደስታ፥
ገታዬና አምላኬ ብሎ።
፬፡ ለኔ ደግሞ የሱስ ሆይ ራራልኝ፤
ያንን ደስታ አትከልክለኝ።
አለማመኔም እንዲጠፋልኝ፥
ቍስሎችህን አሳስበኝ።
ቸሩ አምላክ እኔ ምስኪን ልጅህ፥
ተስፋዬ በአንተ ብቻ ነው።
ኦ ጌታዬ አንተንም የማውቅህ፥
ቍስልህን ስታሳየኝ ነው።
ኦ ጌታዬ አንተንም የማውቅህ፥
ቍስልህን ስታሳየኝ ነው።
፭፡ የተወጋው ልብህ ኦ ቸር መድኅን፤
ያስበኝ በዓለም በረሃ።
በእምነት ልመልከት ቍስልህን፥
በትካዜና በፍስሐ፥
ና አሳርፈኝ በርኅሩኀ ዕቅፍህ፥
አድርሰኝ ወደ የሩሳለም።
ድኜም ፊት ለፊት ኦ ጌታ ልይህ፥
ኦ መድኃኒቴ ኦ አምላኬ።
ድኜም ፊት ለፊት ኦ ጌታ ልይህ፥
ኦ መድኃኒቴ ኦ አምላኬ።