Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 258 ጠባብ ናት ያች የሕይወት ደጅ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ጠባብ ናት ያች የሕይወት ደጅ
መንገድዋም ቀጭን ናት።
ተጋደል አንተ የሰው ልጅ
በዚያ ለመግባት
በዚያ ለመግባት።
፪፡ ሰማይም ገና አልሞላም
ስፍሮች ገና አሉ።
ተከፍተዋል በኢየሱስ ደም
ደጆቹ ለሁሉ
ደጆቹ ለሁሉ።
፫፡ ነጭ ልብስ ለብሰው በሰማያት
ብዙ አእላፋት
ይቆማሉ በዙፋን ፊት።
ላንተም አለ ስፍራ
ላንተም አለ ስፍራ።
፬፡ በሰማይ ቤት በገነቱ
አለ ብዙ ቦታ
ትጠራለህ በወንጌሉ
ወደ ሰማይ ደስታ
ወደ ሰማይ ደስታ።
፭፡ በዚያ አገር በጸጥታ
በምቾት እንድትኖር
ብፁዕ ነህ የምትሰማ
የአምላክን ምክር
የአምላክን ምክር።